በበርካታ ቋንቋዎች ማጭበርበርን ለመለየት፣ ለማስወገድ እና ሪፖርት ለማድረግ አዲስ እርዳታ

አጭበርባሪዎች የእርስዎን ቋንቋ ይናገራሉ። ለዚያም ሲባል ነው FTC አሁን ሪፖርቶችን በበርካታ ቋንቋዎች የሚቀበለው። በማንደሪን፣ ታጋሎግ፣ ቬትናምኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አረብኛ፣ ኮሪያኛ፣ ሩሲያኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ፖላንድኛ እና ሌሎች በርካታ ቋንቋዎች ሪፖርት ለማድረግ ለFTC በ (877) 382-4357 ይደውሉ። አስተርጓሚ ለማናገር 3 ን ይጫኑ። የማንነት ስርቆትን ሪፖርት ለማድረግ፣ በ (877) 438-4338 ይደውሉ እና ለሚፈልጉት ቋንቋ ከምርጫዎቹ ይምረጡ። መስመሮች ከ 9am-5pm የምስራቅ (Eastern) ሰዓት አቆጣጠር ክፍት ናቸው።

Back to top